መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 2፤2013-የአሜሪካ መንግስት ከፍተኛ የጤና ሳይንቲስት አንቶኒዮ ፋውቺ ትራምፕ በምረጡኝ ቅስቀሳቸው እኔን መጥቀሳቸው አሳሳች ነው ሲሉ ተናገሩ

ዶ/ር አንቶኒዮ ፋውቺ የኢንፌክሽን በሽታዎች ተመራማሪ ሲሆኑ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ዙሪያ በተደጋጋሚ ከትራምፕ ጋር ውዝግብ ውስጥ መግባታቸው ይታወሳል፡፡

ትራምፕ ከዶ/ር ፋውቺ ጋር ሲነጋገሩ የሚያሣይ ተንቀሳቃሽ ምስል በፕሬዝዳንቱ የምረጡኝ ቅስቀሳ ላይ ገብቶ መታየቱ ያስቆጣቸው ፋውቺ ንግግራችን ስለ ጤና ነበር ብለዋል፡፡

ለአምስት አስርት ዓመታት በተጠጋ የማህበረሰብ ጤና ግልጋሎት የስራ ዘመኔ ለፖለቲካ ፓርቲ እጩ በአደባባይ ድጋፍ ሰጥቼ አላውቅም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ያለ እኔ ፍቃድ በሌላ ጉዳይ የነበረን ውይይት ትራምፕ ለምርጫ ቅስቀሳ ተጠቅመዋል ሲሉ ተመራማሪው እውነታውን ይፋ አድርገዋል፡፡

21 ቀናቶች በቀሩት የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዶናልድ ትራምፕ የጤናቸው ሁኔታ መሻሻሉን በትላንትናው እለት በቲውተር ገፃቸው ላይ ቲውት አድርገዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *