መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 2፤2013-የኮቪድ 19 ቫይረስ በአንዳንድ ቁሳቁሶች ላይ ለ 28 ቀናት መቆየት እንደሚችል አንድ ጥናት አመላከተ

የአውስትራሊያ ብሄራዊ የሣይንስ ኤጀንሲ እንዳስታወቀው የኮሮና ቫይረስ በገንዘብ ኖት ፣ በእጅ ስልክ ስክሪን እና በማይዝግ የብረት ቁስ ላይ ለ 28 ቀናት ያህል እንደሚቆይ በጥናቴ አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡

ሆኖም በጥናቱ እንደተገለፀው በጨለማ ክፍል ውስጥ ለዚህን ያህል ቀናት ቫይረሱ በነዚህ ቁሳቁሶች ላይ ቢቆይም የፀሃይ ብርሃን ባለበት ስፍራ ቫይረሱ እንደሚሞት መመልከት ተችሏል፡፡

ከዚህ ቀደም በተሰሩ ጥናቶች በገንዘብ ኖት ላይ ከ 2 እስከ 3 ቀናት ፣ በፕላስቲክ እና በማይዝጉ ብረቶች ላይ እስከ 6ቀናት ቫይረሱ ሊቆይ ይችላል የሚለውን ጥናት ውድቅ ያደረገ ሁኗል፡፡

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *