~ በአፍጋኒስታን ሂልማንድ ግዛት በፀጥታ ሃይሎች እና በታሊባን መካከል በተፈጠረ ውጊያ ከ 35 ሺ ያላነሱ ሰዎች ቤት ንብረታቸውን ጥለው መሰደዳቸው ተሰማ፡፡
~ በአዘርባጃን አርሜንያ በናጎርኖ ካራባክ ግዛት በቀጠለው ግጭት የተነሳ ከፍተኛ የሰብዓዊ ቀውስ እየተፈጠረ ይገኛል፡፡
~ ሩዋንዳ ለአደንዣዥ እጽ ጥቅም ላይ የሚውለውን ካናቢስ ለህክምና ተግባር እንዲውል ፍቃድ መስጠቷ ተሰማ፡፡
~ የሞዛምቢክ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር አርሚንዶ ቲያጎ በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸው ተሰማ፡፡ ሚኒስትሩ በመኖሪያ ቤታቸው ራሳቸውን አግለዋል፡፡
~ የአሜሪካ የፌደራል የምርመራ ቢሮ /FBI/ በቤሩት በወርሃ ነሀሴ ካጋጠመው ፍንዳታ ጋር በተያያዘ በመነሻው ዙሪያ ድምዳሜ ላይ መድረስ አለመቻሉን አሣወቀ፡፡ በቤሩት ፍንዳታ 200 የሚጠጉ ሰዎች ህይወታቸውን ማጣታቸው ይታወሳል፡፡
~ በሜክሲኮ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ የሟቾች ቁጥር ከ 84ሺ መብለጡን የjoን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ ይፋ አደረጉ፡፡
~ የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ አን በጎርፍ አደጋ የተነሳ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ስፍራ እንዲያገግም በቀጣዮቹ 5 ዓመታት 25 ሺ መኖሪያ ቤቶች መገንባታቸው ተሰማ፡፡
በስምኦን ደረጄ