መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 11፤2013-የብስራት ማለዳ አጫጭር ዓለምአቀፍ መረጃዎች

🇸🇴የሶማሊያ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር አህመድ ኢሳ አዋድ ከስልጣን ተነሱ።አምባሳደር ተደርገው እንደሚሾሙ ቢነገርም በቲውተር ገፃቸው ዝግጁ አለመሆናቸውን ተናግረዋል።ከስልጣን የተነሱበት ጉዳይ ግልፅ ባይደረግም በትግራይ ካለው ቀውስ ጋር በተያያዘ እንደሆነም ተሰምቷል።

🇰🇪የኮቪድ 19 መዛመት ቢቀጥልም ኬንያ ከአበባ ሽያጭ የምታገኘው ገቢ መጨመሩን አስታወቀች።በ10 ወራት ውስጥ 1.1 ቢሊዮን የአሜርካን ዶላር ዋጋ ያለው ምርት የተላከ ሲሆን ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነፃፀር የ9በመቶ ብልጫ ተመዝግቧል።ኬንያ ከሻይ ምርት በመቀጠል አበባ ከፍተኛ ገቢ ያስገኝላታል

🇲🇿በሞዛምቢክ የፖሊስ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ውስጥ 15 ተማሪዎች ነፍሰጡር መሆናቸውን ተከትሎ ሁለት አስተማሪዎች መታሰራቸው ተሰማ።ተማሪዎቹ በመምህራኑ ወሲባዊ ጥቃት ሰለባ ነበሩ ተብለዋል

🇦🇿የአዘርባጃን ጦር ሶስት አውራጃዎችን መቆጣጠሩ ተሰማ።አርሜኒያ ግዛቶችን ለመመለስ መስማማቷን ተከትሎ የአርሜኒያ ነዋሪዎች ይኖሩበት የነበረውን ቤት እያቃጠሉ ከስፍራው እየለቀቁ ይገኛል።

🇳🇪በህንድ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር ከ9ሚሊየን መብለጡ የተሰማ ሲሆን 132,162 ሰዎች በቫይረሱ ህይወታቸውን አጥተዋል።

🇲🇽በሜክሲኮ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ100ሺ መብለጡ የተሰማ ሲሆን በቫይረሱ በመላው ዓለም ህይወታቸውን ካጡት መካከል 7በመቶ ያህሉ በሜክሲኮ መሆናቸው ሪፖርት ተደርጓል።

🇺🇸🇨🇳በእስያ ፓስፊክ ጉባኤ ላይ በዛሬው እለት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው አቻቸው ሺ ጂፒንግ በቨርቹአል ውይይት ይሳተፋሉ።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *