መደበኛ ያልሆነ

ጥር 4፤2013 – በአዲስ አበባ ከተማ አንዳንድ አካባቢዎች በቀጣዮቹ ሶስት ቀናት የኃይል አቅርቦት ይቋረጣል!

ረቡዕ ጥር 5 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 እስከ ቀኑ 8:00 ድረስ

• በጎተራ ፣ በፔፒሲ ፋብሪካ ፣ በጎፋ ማዞርያ ፣ በፅጌ ሆቴል ፣ በቄራ ፣ በአስቴር ቡና ፣ በፒኮክ ፣ በግሎባል ሆቴል ላንቻ ፣ በጨርቆስ ቤ/ክ እና አካባቢዎቻቸው የኀይል አቅርቦት እንደሚቋረጥ ብስራት ራዲዮ ሰምቷል።

በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 1:00 እስከ ቀኑ 10:00 ድረስ
• በሳሪስ አቦ ቤ/ክ፣ በቦሌ ቡልቡላ ኮንደሚኒየም፣ በቡልቡላ ማርያም ማዞርያ፣ በክሬሸር እና አካባቢዎቻቸው

ሐሙስ ጥር 6 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 እስከ ቀኑ 5:00 ድረስ
• በኬንያ፣ በእንግሊዝ እና በእስራኤል ኤምባሲዎችና አካባቢዎቻቸው፣

በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 1:00 እስከ ቀኑ 9:00 ድረስ፣
• በግሎባል ሆቴል ላንቻ፣ በጨርቆስ ቤ/ክ፣ በአዲስ ሰፈር፣ በኢንዱስትሪ መንደር፣ በሀኪም ማሞ፣ በዮሴፍ ቤ/ክ እና አካባቢዎቻቸው፣

እንዲሁም አርብ ጥር 7 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 እስከ ቀኑ 9:00 ድረስ፣
• በቦሌ ሚካኤል፣ በቦሌ ካርጎ፣ በማዕድን ማህበር፣ በሀግቤስ፣ በአዲሱ ሚካኤል፣ በፓውሎስ ሆስፒታል፣ በሞተራ ሆቴል፣ በጨው በረንዳ፣ በመርካቶ እስከ ሰባተኛ እና አካባቢዎቻቸው፣

በመካከለኛ የኤሌክትሪክ ተሸካሚ መስመር ላይ የማሻሻያ ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥ በመሆኑ ፤ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *