መደበኛ ያልሆነ

ጥር 4፤2013-ንቅሳት(ታቱ) ተሰርቶ ሂሳብ ያልከፈለውን ወጣት በፕላስቲክ መጠቅለያ ከዛፍ ጋር እንዲጠቀለል ተደረገ

በቬትናም ሀኖይ ነዋሪ የሆነዉ ወጣቱ በእጆቹ ላይ የንቅሳት ሥራ ከተሠራ በኃላ ለመክፈል የሚጠበቅበትን ገንዘብ ሳይከፍል ያመልጣል ፡፡ ለቀናት በእንዲህ አይነቱ ሁኔታ ከተደባበቀ በኃላ በስተመጨረሻ ታቱን የሰራለት ሰዉ ጋር ይገናኛል ፡፡

ልብሱን በሀይክ በማስወለቅ፣ በፕላስቲክ ከዛፍ ጋር መጠቅለል ለማሰር እንደተገደዱ ታቱን የሰሩለት ቲ የተባሉ ግለሰብ ተናግረዋል፡፡

ለታቱ ለመክፈል ጥላቻ አሳይቻለዉ የሚል ጹሁፍ በደረቱ ላይ እንዲለጠፍ ያደረጉት ቲ ሌሎች ከእርሱ እንዲማሩ ለማሳየት ነዉ እንጂ ምሬዋለሁ ሲሉም ተደምጠዋል፡፡

በቬትናም ሀኖም ከባድ ቅዝቃዜ የሚመዘገብበት ወቅት ሲሆን ከ10 ዲግሪ ሴልሼየስ በታች ይገኛል፡፡ድርጊቱ በማህበራዊ ገጽ ትስስር መነጋገሪያ ሆኗል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *