መደበኛ ያልሆነ

ጥር 4፤2013 -ንብረትነቱ የስሪዊጃያ አየር መንገድ የሆነዉና ባሳለፍነዉ ቅዳሜ የተከሰከሰዉ አውሮፕላን ከጥቁር ሣጥኖቹ መካከል አንዱ ተገኘ

የኢንዶኔዥያ ባለሥልጣናት ቅዳሜ እለት በጃቫ ባሕር ከወደቀው የስሪዊጃያ አየር መንገድ አውሮፕላን አንድ ጥቁር ሳጥን ማግኘታቸውን የባህር ኃይሉ ቃል አቀባይ በዛሬዉ እለት ተናግረዋል ፡፡

የበረራ ሁነቱን የመቅጃ መሣሪያው ወደ ጃካርታ ወደብ እየተጓጓዘ መሆኑን ቃል አቀባዩ ፋጃራ ትሪ ሮሃዲ ለሮይተርስ ተናግረዋል፡፡

የኢንዶኔዥያ የሀገር ዉስጥ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች አስቀድመዉ ይህንኑ መሣሪያ በፍጥነት በሚጓዝ ጀልባ ላይ ተጭኖ ሲንቀሳቀስ አሳይተዋል፡፡

የየተገኘዉ ሣጥን የአውሮፕላኑ የበረራ መረጃ መቅጃ ይሁን ወይም የኮክፒት(የአብራሪዎች ክፍል) የድምፅ መቅጃ መሆኑ ግን አልተገለጸም ፡፡

62 መንገደኞችን ያሳፈረዉ ቦይንግ 737-500 አውሮፕላን ከጃካርታ አውሮፕላን ማረፊያ ከተነሳ ከአራት ደቂቃዎች በኋላ ቅዳሜ ዕለት ጃቫ ባሕር ዉስጥ መከስከሱ ይታወሳል፡፡

በሚኪያስ ጸጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *