መደበኛ ያልሆነ

ጥር 4፤2013-አንድ ጥፊ ለፕሬዝዳንትነት ያበቃል

በምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር ዩጋንዳ የፊታችን ሀሙስ ምርጫ ይደረጋል፡፡ይህ ምርጫ የአዛዉንቱ ዩዌሪ ሙሴቬኒ እና የወጣቱ ድምጻዊ ቦቢ ዋይን ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ፡፡አጭር መረጃ ስለ ሁለቱ መሪዎች፡-

ቦቢ ዋይን ፡-የ38 ዓመቱ ወጣት ድምጻዊ ቢቢ ዋይን(የመድረክ ስሙ ነዉ) ከደሃ ቤተሰብ የተገኘ በችግር ተከቦ ያደገ ነዉ፡፡ወላጅ እናቱን ገና በለጋ እድሜዉ የተነጠቀ ሲሆን ወደ ሙዚቃዉ ዓለም ከገባ በኃላ የፍቅር ሙዚቃዎችን በማቀንቀን ከፍተኛ ተወዳጅነትን አገኘ፡፡በአንዱ ምሽት ግን አንድ የዩጋንዳ ፖሊስ ያለጥፋቱ በጥፊ ይመታዋል፡፡በዚህ የተበሳጨዉ ቦቢ ዋይን መንግስትን መቃወም፣የጸጥታ አካላት ጉልበተኛነትን ማዉገዝ ጀመረ፡፡ዛሬ ሚሊየኖች የሚከተሉት ለሙሴቬኒ የሚያሰጋ ፖለቲከኛ ሲሆን ወደ ማህበራዊ ፍትህ አንቂነት የተቀላቀለዉ የዛች ምሽት ጥፊ መዘዝ ነበር፡፡ምናልባትም አዲሱ የዩጋንዳ ፕሬዝዳንት ሊሆን እንደሚችል ይጠበቃል፡፡

ዩዌሪ ሙሴቬኒ፡-ለ35 ዓመታት በስልጣን ላይ የቆዩ ሲሆን ዛሬም ስልጣናቸዉን ላለመነጠቅ የሞት ሽረት ትግል እያደረጉ ይገኛል፡፡ሙሴቬኒ ለወንድ ልጃቸዉን ከፍተኛ ሹመት የሰጡ ሲሆን በዩጋንዳ ህግ መሰረት በህገ መንግስቱ ከ75 ዓመት በላይ የሆነ ሰዉ ለፕሬዝዳንትነት እንዳይወዳደር የሚለዉን ህግ አሰርዘአዉ ለምርጫ ቀርበዋል፡፡ወደ ስልጣን ሲመጡ የሎርድ ሬዚስታን አርሚ ቡድን ደምስሰዉ የጨፍጨፉዎቹን ኢዳሚን ዳዳና አቦቴ ታሪክ የቀየሩ ቢሆን 80በመቶ የዩጋንዳ ህዝብ በስልጣን ወንበሩ ላይ ከእሳቸዉ ዉጪ ማንም አይቶ አያዉቅም፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *