መደበኛ ያልሆነ

ጥር 4፤2013-የማላዊ ፕሬዝዳንት ከድምጻዊቷ ማዶና ጋር የነበራቸው ቆይታ ያስከተለባቸውን ትችት ተከትሎ ይቅርታ ጠየቁ

የማላዊ ፕሬዝዳንት ላዛሩስ ቻካዌራ በሀገሪቱ በቅርቡ በጨመረዉ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መባባስ ክሶች ውስጥ ለተፈጠረው ችግር ተጠያቂ ከሆኑት መካከል መሆናቸዉ ተገለጸ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ባለፈው ሳምንት ከአሜሪካዊቷ የፖፕ ድምጻዊት ማዶናን ሲገናኙ የሚያሳዩ ምስሎች እና ቪዲዮዎች በተሰራጩበት ጊዜ እጃቸውን እርስ በእርስ በመጨባበጥ እና አፍና አፍንጫ ሳይሸፍኑ ታይተዋል፡፡ በተጨማሪም ማህበራዊ ርቀትን ሳይጠብቁ ሲንቀሳቀሱ ፕሬዝዳንቱ ተስተዉለዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ለድርጊታቸዉ ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡በማላዊ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸዉን የሚያ ሰዎች በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ ሲሆን ባሳለፍነዉ ሳምንት በሀገሪቱ እዉቅ ፖለቲከኛን ጨምሮ የሚዲያ ሰዎች በቫይረሱ ህይወታቸዉን አጥተዋል፡፡

በ2020 ዓመት በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡት ቻካዌራ የምርጫዉን ስኬት ተከትሎ ማላዊን የአለማችን የዓመቱ ምርጥ ሀገር ተብላ እንድትመረጥ ማስቻሉ አይዘነጋም፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *