መደበኛ ያልሆነ

ጥር 4፤2013-የትራምፕ ደጋፊዎች ሁከት ሊፈጥሩ ይችላሉ ሲል ኤፍ.ቢ.አይ አስጠነቀቀ

የአሜሪካ ተመራጩ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ፕሬዝዳንት ሆነው በዓለ ሲመት ከመፈጸማቸዉ በፊት ባሉት ቀናት በመላው አሜሪካ የታጠቁ የተቃውሞ ሰልፎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ኤፍ.ቢ.አይ አስጠንቅቋል፡፡

ከበዓለ ሲመቱ አስቀድሞ የታጠቁ ቡድኖች በአምሳ የሜሪካ ግዘዛቶች መዲና እና በዋሽንግተን ዲሲ ለመሰብሰብ እቅድ እንዳላቸዉ የፌደራሉ የምርመራ ቢሮ ሪፖርት ደርሶኛል ሲል አስጠንቅቋል፡፡

ስጋቱ የመጣዉ በዓለ ሲመቱ በራሱ ጠንካራ የደህንነት ስራ የሚያስፈልገዉ በመሆኑ የተነሳ ነዉ።

ባይደን እና ምክትላቸዉ ካማላ ሀሪስ በካፒቶል ሕንፃ ዉጪ ሆነው ቃለ መሃላ ይፈፀማሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ከቀናት በፊት ጽንፈኛ የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች ደም አፍሳሽ ግጭት በአካባቢዉ ማስነሳታቸዉ ይታወሳል፡፡

በበዓለ ሲመቱ እለት ደህንነቱን ለማጠናከር እስከ 15,000 የሚደርሱ የብሔራዊ ጥበቃ ወታደሮች ሊገኙ እንደሚችሉ ይጠበቃል፡፡

በሚኪያስ ጸጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *