መደበኛ ያልሆነ

ዛሬ ጥር 4፤2013-የትራምፕ አስተዳደር ኩባን ሽብርን ድጋፍ ታደርጋለች ሲል ሰየመ

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ዋና ጸሀፊ ማይክ ፖምፒዮ እንዳስታወቁት ኩባን ሽብርተኝነት ስፖንሰር ታደርጋለች ሲል መንግስታቸዉ መሰየሙን ይፋ አድርገዋል፡፡ በትራምፕ አስተዳደር የመጨረሻ ቀናት ውስጥ የቅርብ ጊዜ እርምጃ ታዛቢዎች እንደሚሉት የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የውጭ ፖሊሲ ዕቅዶችን የሚያወሳስቡ ሆነዋል፡፡

ፖምፒዮ በሰጡት መግለጫ አሜሪካ ኩባን በዚህ ዝርዝር የሰየመችዉ ለአሸባሪዎች አስተማማኝ ከለላ በመስጠት እና ለዓለም አቀፍ ሽብርተኝነት ደጋግማ ድጋፍ በማድረጓ ነዉ ብለዋል ፡፡

በተጨማሪም ኩባ በቬንዙዌላ እና በምዕራባዊ ንፍቀ ክበብ ውስጥ ጣልቃ ገብነት ታደርጋለች ሲሉ ፖምፒዮ ከሰዋል፡፡

በዚህ እርምጃ የኩባን መንግስት ተጠያቂ ከማድረግ ባለፈ ግልጽ መልእክት እናስተላልፋለን ያሉት ፖምፒዮ የካስትሮ አገዛዝ ዓለም አቀፍ ሽብርተኝነትን እና የአሜሪካን ፍትህ ለማፈራረስ የሚያደርገውን ድጋፍ ማቆም አለበት ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ከዘጠኝ ቀናት በኃላ በዓለ ሲመታቸዉን የሚፈጽሙት ባይደን ዋሽንግተንን ከሃቫና ጋር የተሻለ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ለመመስረት እቅድ እንዳላቸዉ ብሉምበርግ በዚህ ወር መጀመሪያመዘገቡ ይታወሳል፡፡የጉዞ ፣ የኢንቨስትመንት እና የገንዘብ ማስተላለፍ እገዳዎችን ጨምሮ ለማንሳት የባይደን አስተዳደር ዉጥን አለዉ፡፡

የኦባማ አስተዳደር ኩባን ከአሜሪካ የሽብርተኝነት ስፖንሰር አድራጊዎች ዝርዝር ውስጥ ማስወገዱ የሚታወስ ሲሆን ሆኖም ግን የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በኩባ መንግስት እና በአገሪቱ ውስጥ ባሉ የተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ላይ ጫና ሲያሳድር ቆይቷል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *