
የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ለወባ ምርመራ አገልግሎት የሚውሉ ማይክሮስኮፖችን ከታህሳስ 7 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ማሠራጨቱን ከመጋዘን አያያዝና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ማይክሮስኮፖቹ 439 ሲሆኑ በጤና ተቋማት ጥራቱ የተጠበቀ ምርመራና የህክምና አገልግሎት ለተጠቃሚው ህብረተሰብ ለመስጠት እንደሚያገለግሉ ተገልጿል፡፡
ስርጭቱም ለኦሮምያ ፣ ለአማራ ፣ ለደቡብ ብሔር ብሔረሠቦችና ሕዝቦች ፣ ለሶማሌ ፣ ለአፋር ፣ ለቤንሻንጉል ጉሙዝና ለጋምቤላ ክልል ጤና ቢሮዎች ተካሂዷል።
16 ሚሊዮን 340 ሺህ 416 ብር ወጪ እንደተደረገባቸውም ኤጀንሲው በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ አስፍሯል።