መደበኛ ያልሆነ

ጥር 5፤2013-ኢራን አጭር ርቀት የሚምዘገዘግ ሚሳኤል አስወነጨፈች

በኢራን መንግሥት እና በዋሽንግተን መካከል ያለዉ ውጥረት በከፍተኛ ደረጃ በጨመረበት በዚህ ጊዜ ኢራን በዛሬዉ እለት ረፋድ ላይ የአጭር ርቀት የባህር ኃይል ሚሳኤል ሙከራ አድርጋለች፡፡

ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ ከሚገኙ ሀገራት የተሻለ የሚሳኤል ግንባታ አቅም ላይ የደረሰች ሲሆን በአሜሪካ እና ጠላት ሀገራት በምትላቸዉ ሊነሳ የሚችል ስጋትን ለመከላከል ሀይሏን እያጠናከረች ትገኛለች፡፡

ምዕራባውያኑ የኢራን ሚሳኤሎችና የኒዉክሌር ግንባታዋ ለአከባቢ አለመረጋጋት ምክንያት ናቸዉ ሲሉ ይከሳሉ፡፡

ኢራን በጀመረችዉ የሁለት ቀን ወታደራዊ ልምምድ ማክራን ከተሰኘዉ ግዙፍ የጦር መርከብ ዜሪ የተባለ ሚሳኤልን በኦማን ባሕረ ሰላጤ አስወንጭፋለች፡፡

የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በ2015 ከተደረሰበት የቴህራን የኒወክሌር መርሃ ግብር ስምምነት አሜሪካ እንድትወጣ በማድረጉ በቴህራንና በዋሽንግተን መካከል ያለዉ ዉዝግብ እንዲካረር ምክንያት ሆኗል፡፡

በሚኪያስ ጸጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *