መደበኛ ያልሆነ

ጥር 5፤2013-ኢንዶኔዥያ የኮሮና ቫይረስ የክትባት መድሃኒቱን ቅድሚያ ለወጣቶች እሰጣለሁ ማለቷ ጥያቄን አስነሳ

በህዝብ ብዛቷ ከዓለም በአራተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ኢንዶኔዥያ ቅድሚያ በመስጠት ለመከተብ ያሰበችው ከፍተኛ የስራ ሃይል የሆነውን የህብረተሰብ ክፍል መሆኑን አስታውቃለች፡፡

እድሜያቸው ከ 18 እስከ 59 ያሉት የሀገሪቱ ዜጎች በቻይና የተሰራውን ሲኞቫክ የክትባት መድሃኒት ያገኛሉ ተብሏል፡፡

የኢንዶኔዥያ የጤና ሚኒስቴር እንደሚለው ቫይረሱን ቤት ውስጥ ወዳሉ አዛውንቶች ይዘው ሊሄድ የሚችሉት ወጣቶች በመሆናቸው ቅድሚያ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡

ቢልም ሂደቱ ያልተለመደ በሚል ጥያቄ አስነስቷል፡፡ በእንግሊዝ የመጀመሪያ ክትባቱን የወሰዱት የ 90 ፣ በካናዳ የ89 ፣ በጀርመን የ 101 ዓመት እድሜ ያላቸው አዛውንቶች እንደነበሩ አይዘነጋም፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *