መደበኛ ያልሆነ

ጥር 5፤2013-ፕሬዝዳንት ፑቲንን በመተቸት የሚታወቀዉ አሌክሲ ናቫሊን እሁድ ወደ ሩሲያ ሊያቀና መሆኑ ስጋትን ፈጥሯል

የፑቲን አስተዳደር በመተቸት የሚታወቀዉ አሌክሲ ናቫልኒ በዛሬዉ እለት እንዳስታወቀዉ በሩሲያ ሊታሰር እንደሚችል ቢያምንም የፊታችን እሁድ ወደ ሩሲያ እንደሚመለስ ተናግሯል፡፡

ነርቭን በሚጎዳ ኖቪቾክ ንጥረ ነገር መመረዙን ተከትሎ ባሳለፍነዉ ነሀሴ ወር ወደ ጀርመን ያመራዉ ናቫሊን በድጋሚ ወደ ሩሲያ እመለሳለሁ ማለቱ ስጋት ፈጥሯል፡፡

በሶቬቶች ዘመን በስፋት ጥቅም ላይ ይዉል የነበረዉ ኖቪቾክ የተባለዉ ነርቭን የሚመርዝ ንጥረ ነገር ለአሌክሲ ናቫሊን በመስጠት እንዲመረዝ ያደረገዉ የሩሲያ መንግስት ነዉ የሚል ክስ ቢቀርብም ክሱን መንግስት ያጣጥለዋ፡፡

ይህ ንጥረ ነገር ጥቅም ላይ እንዳይዉል መከልከሉ ይታወሳል፡፡ወደ ሀገሬ ተመልሼ በወርሃ መስከረም በሚካሄደዉ የህዝብ እንደራሴ ምክር ቤት ምርጫ እሳተፋለዉ የሚለዉ ናቫሊን በሩሲያ መንግስት ዘነድ ክስ ተመስርቶበታል፡፡

ሆኖም የሩሲያ መንግስት በማንኛዉም ጊዜ ወደ ሀገሩ መግባት ይችላል ሲል አስታዉቋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *