መደበኛ ያልሆነ

ጥር 6፤2013-ሱዳን የኢትዮጵያ አውሮፕላን ድንበሬ አቋርጧል ስትል ተናገረች

የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው አንድ የኢትዮጵያ አውሮፕላን ድንበሩን አቋርጦ መግባቱን ይፋ በማድረግ አደገኛ እና ተገቢ ያልሆነ ሲል ገልጾታል፡፡

የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ድርጊቱ አደገኛ ደግሞም በድንበር አከባቢው ያለዉን ውጥረትን ሊያባብስ ይችላል ሲል አስታዉቋል፡፡

ሱዳን አደገኛ ዉጥረቱ እንዳይባባስ እንዲህ ዓይነት ድርጊት መደገም የለበትም ስትል መጠየቋን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል ፡፡

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሱዳን ታጣቂ ኃይሎች የእርሻ ስፍራዎችን በመውረርና ንብረቶችን በመዝረፍ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት መግባታቸውን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

ሱዳን እና ኢትዮጲያ 750 ኪ.ሜ ድንበር የሚጋሩ ሲሆን ባለፉት ዓመታት በተለይም በአል-ፋሻጋ አከባቢ ግጭቶች የተለመዱ ናቸው ፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *