
ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ ታሪክ ለሁለተኛ ጊዜ የተወነጀሉ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት ሆነዋል።
የዝህብ እንደራሴዎቹ ትራምፕ ምርጫው ተጭበርብሯል ሲሉ ደጋፊዎቻቸውን ለአፅመ ጋብዘዋል ሲሉ ከሰዋቸዋል፡፡
አሁን በህግ መወሰኛው ምክር ቤት ለፍርድ የሚቀርቡ ሲሆን ፣ ነገር ግን በቀጣይ ሳምንት ነጩን ቤተ-መንግስት መልቀቃቸውን ተከትሎ እውን የሚሆን ነው፡፡
የምክር ቤቱ አባላት ዳግም ለምርጫ እንዳይወዳደር ድምፅ የሚሰጡም ይሆናል፡፡ በምክር ቤቱ ድምፅ መሰጠቱን ተከትሎ በቪዲዮ የታገዘው ምስል ላይ ትራምፕ ፣ ስለ ተመሰረተባቸው ክስ ሳይጠቅሱ ደጋፊዎቻቸውን ሰላም እንዲያወርዱ ብቻ ጠይቀዋል፡፡
‹‹አመፅ እና ጥፋት በእኛ ሀገር ቦታ የለውም፡፡ የኔ እውነተኛ ደጋፊዎች ይህን አያደርጉም‹‹ ሲሉም ተደምጠዋል፡፡
በሚኪያስ ፀጋዬ