መደበኛ ያልሆነ

ጥር 6፤2013-የትዊተር ዋና ስራ አስፈጻሚ የትራምፕ መታገድ ትክክለኛ ውሳኔ ቢሆንም አስፈሪ ሲሉ ገለጹት

የትዊተር ዋና ስራ አስፈጻሚ ጃክ ዶርሴ እንደተናገሩት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን ማገድ ትክክለኛ እርምጃ ነበር ብለዋል፡፡ሆኖም ግን የትራምፕ ቋሚ እግዳ ያልተለመደ ዓይነት ሲሉ ተነግረዋል፡፡

እገዳው ጤናማ ውይይት ለማጎልበት በቂ ሥራን ትዊተር እንዳልሰራ ማሳየቱ ውድቀት ነው ሲሉ ጃክ ዶርሴ ገልጸዉታል፡፡ትዊተር የትራምፕን አካውንት በማገዱ የሚያመሰግኑ እንዳሉ ሁሉ በርካታ ትችቶች እየቀረቡበት ይገኛል፡፡

የጀርመኗ ቻንስለር አንጌላ መርኬል ቃል አቀባይ የማህበራዊ ሚዲያ እገዳን ችግር ያለበት ሆኖ አግኝቸዋለሁ ሲሉ የሜክሲኮ ፕሬዝዳንት ማንም ሰው ሳንሱር ሲደረግ አልወድም ሲሉ መናገራቸዉ ተደምጧል ፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *