መደበኛ ያልሆነ

ጥር 6፤2013-የኔቫዳ ግዛት የተወካዮች ምክርቤት አባል ነበረው ትውልደ ኢትጵያዊው አሜሪካዊው አሌክሳንደር አሰፋ በማጭበርበር ወንጀል ከምክርቤት አባልነቱ እንዲለቅ ተደረገ፡፡

አሌክሳንደር ምክርቤቱን እንዲለቅ ያስገደዱት ምክንያቶች በምረጡኝ ዘመቻ ወቅት የተዋጣለትን ገንዘብ መዋጮ ባልተገባ መልኩ ለግል ጥቅሙ አውሏል በሚል ምክንያት ነው።

በምርጫው አግባብበነት በሌለው መኖሪያ አድራሻ ተወዳድሯል ፣የተሳሳተ የጋብቻ ማስረጃ አቅርቧል እና አጭበርብሯል በሚሉ ተጨማሪ ምክንያቶች ከምክር ቤቱ እንዲለቅ ተገዷል ፡፡

ፖሊስ በርከት ተደራራቢ ጥፋቶች ክስ እንደሚመሰርትበት ይጠበቃል።

አሌክሳንደር የዲሞክራቲክ ፓርቲን ወክሎ በኔቫዳ ግዛት ተወካዮች ምክርቤት የዲስትሪክት 42 ተመራጭ በመሆን ለሁለት የስራ ዘመን የምክርቤቱ አባል በመሆን ቆይቷል።

አሌክሳንደር በላስቬጋስ እና በአካባቢው የኢትዮጵያን ኮሚኒቲ ላቅ ያለ ተሳትፎ እና አገልግሎት የነበረው ሲሆን ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጰያውያን አንዲሁም በምርጫ የወከለውን የማህበረሰብ ክፍል በታታሪነተት እና በታማኝነት ሲገለግል ቆይቷል፡፡

የ 38 አመቱ ጎልማሳ አሌክሳንደር በላስቬጋስ ከተማ የኢትጰያውያን የንግድ ተቋማት በብዛት የሚገኙበት መንደር ሊትል ኢትዮጵያ ተብሎ በይፋ እንዲሰየም በግንባር ቀደምትነት ሲሰራ ቆየ የምክር ቤት አባል ነው፡፡

ኢትዮጰያ ውስጥ በዶዶላ ከተማ ተወልዶ ያደገው ኤከልሳንደር አውሮፕላን የማብረር የካፒቴንነት ፈቃድ ያለው ሲሆን በ ምፖለቲካል ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪውን በቨርጂኒያ ግዛት ከሚገኘው ከአቨርት ዩኒቨርስቲ አግኝቷል አማርኛ ኦሮምኛ እና እንግሊዘኛ ቋንቋዎችን ይናገራል።

ዳንኤል ገብረማሪያም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *