መደበኛ ያልሆነ

መጋቢት 28፣2013-ሰሜን ኮርያ አትሌቶቿን ከኮሮና ቫይረስ ለመጠበቅ ስትል በኦሎምፒክ ዉድድር እንደማትሳተፍ አስታወቀች

ሰሜን ኮርያ ይህንን ዉሳኔ ያሳለፈችዉ አትሌቶቿን ከኮሮና ቫይረስ ለመከላከል ስትል በቀጣዩ ክረምት በቶኪዮ አስተናጋጅነት በሚካሄደዉ የኦሎምፒክ ውድድር እንደማትሳተፍ አስታዉቃለች፡፡በወረርሽኙ የተነሳ በኦሎምፒክ ለመሳተፍ እቸገራለሁ ያለች የመጀመሪያዋ ሀገር ሰሜን ኮርያ ሆናለች፡፡

በሰሜን ኮርያ በኮሮና ቫይረስ የተጠቃ ሰዉ እንዳለ ሀገሪቱ እስካሁን ድረስ አላስታወቀችም፡፡በሁለቱ ኮርያዎች መካከል ያለዉን የሁለትዮሽ ግንኙነት በውድድሩ ሰሞን ለማጠናከር የነበረዉን ዉጥን ያስቀራል፡፡

በ2018 ዓመት በደቡብ ኮርያ ተዘጋጅቶ በነበረዉ የጸደይ ኦሎምፒክ ሰሜን ኮርያ 22 አትሌቶቿን ወደ ሴኦል በጊዜዉ ልካ ነበር፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *