መደበኛ ያልሆነ

መጋቢት 28፣2013-ሳዑዲ አረቢያ የኮሮና ቫይረስ በሽታን የመከላከል አቅም ያላቸዉ ሰዎች ወደ መካ ማቅናት እንደሚችሉ ፈቀደች

በተያዘዉ ዓመት ዑምራ ማድረግ እንደሚቻል የሳዑዲ አረቢያ መንግስት ፍቃድ የሰጠ ሲሆን በሽታዉን የመከላከል አቅም ላላቸዉ ሰዎች ብቻ መፈቀዱን አስታውቋል፡፡ በዚህ መሰረት የኮሮና ቫይረስ የክትባት መድኃኒት መዉሰድ ዋንኛዉ መስፈርት ሆኗል፡፡

ተጓዦች ሁለት ዶዝ ያለዉን የኮሮና ቫይረስ ክትባት መዉሰድ ይኖርባቸዋል፡፡አልያም አንድ ዶዝ ብቻ የወሰዱ ከሆነ ከወሰዱ ከ14 ቀናት በኃላ መምጣት ይችላሉ ተብሏል፡፡በሳዑዲ አረቢያ በወረርሽኙ የተነሳ ከ6700 በላይ ሰዎች ህይወታቸዉን አጥተዋል፡፡

ባለፈዉ ዓመት በሀጅ ስነስርዓት ለመገኘት የተፈቀደላቸዉ 10ሺ ያህል ሰዎች ሲሆኑ በሳዑዲ ለሚኖሩ ዜጎች ብቻ የተፈቀደ ነበር፡፡በ2019 በሀጅ ስነስርዓት ላይ ከመለዉ ዓለም የተዉጣጡ 2.5 ሚሊየን ሙስሊሞች መገኘታቸዉ ይታወሳል፡፡

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *