መደበኛ ያልሆነ

መጋቢት 28፣2013-በናይጄሪያ ከ1800 በላይ ታራሚዎች ማረሚያ ቤት ሰብረዉ ማምለጣቸዉ ተሰማ

በደቡብ ምስራቃዊ ናይጄሪያ ኦዊሪ በተባለች ከተማ በሚገኘዉ ማረሚያ ቤት ላይ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ከ1800 በላይ ታራሚዎች አምልጠዋል፡፡ከማረሚያ ቤት ካመለጡት መካከል ስድስቱ ሲመለሱ 35 ያህሉ ለማምለጥ ፍቃደኛ እንዳልነበሩ ተሰምቷል፡፡

ከማረሚያ ቤቱ ለማስመለጥ ተግባሩን የፈጸመዉ አካል ፖሊስ እንዳስታወቀዉ ከሆነ የቢያፍራ የተገንጣይ ሀይሎች ላይ መንግስት ጣቱን ሲቀስር ቡድኑ ግን አስተባብሏል፡፡የቢያፍራ ተገንጣይ ሀይሎች ጥቃቱን በእኛ ላይ መሳበቡ ዉሸት ነዉ ሲል አጣጥሎታል፡፡

በአጠቃላይ ከማረሚያ ቤቱ ያመለጡ ሰዎች ቁጥር 1‚844 ያህል መሆናቸዉን የናይጄሪያ የማረሚያ ቤት አስተዳደር አስታዉቀዋል፡፡ታራሚዎችን ከማረሚያ ቤት ለማስመለጥ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጥቃት ተፈጽሟል፡፡

ድርጊቱን ተከትሎ የናይጄሪያዉ ፕሬዝዳንት ሙሃሙድ ቡሃሪ የሽብርተኝነት ተግባር እንዲሁም ስርዓት አልበኝነት ሲሉ ገልጸዉታል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *