መደበኛ ያልሆነ

መጋቢት 28፣2013-ፑቲን እስከ 2036 ድረስ በስልጣን ላይ የሚያቆያቸዉን ህግ በፊርማቸዉ አጸደቁ! አሌክሲ ናቫሊን በኮሮና ቫይረስ ተጥቅቶ ከማረሚያ ቤት ወደ ህክምና ስፍራ ማምራቱ ተሰምቷል!

የሩሲያዉ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በክርምሊን ቤተመንግስት እስከ በፈረንጆቹ ዘመን አቆጣጠር እስከ 2036 ድረስ በስልጣን ላይ መቆየት የሚያስችላቸዉን ህግ በትላንትናዉ እለት ፈርመዋል፡፡

በጸደቀዉ ህግ መሰረት ፑቲን በ2024 እና በ2030 በሚደረገዉ ምርጫ በድጋሚ በመወዳደር ለሁለት የስራ ዘመን በስልጣን ላይ እንዲቆዩ የሚያስችላቸዉ ነዉ፡፡ባለፈዉ ዓመት ፑቲን የስልጣን ዘመናቸዉን ለማራዘም የሀገሪቱ ህግ እንዲሻሻል ማድረጋቸዉ አይዘነጋም፡፡

የስልጣን ዘመን ማራዘሚያዉን ተከትሎ 68ኛ ዓመታቸዉ ላይ የሚገኙት ፑቲን እስከ 83 ዓመታቸዉ ድረስ ሩሲያን በፕሬዝዳንትነት ለመምራት እቅድ ይዘዋል፡፡ፑቲን በስልጣን ላይ ለመቆየት በሚል ህግ ማሻሻላቸዉን ተቃዋሚዎቻቸዉ በህገ መንግስቱ ላይ የተደረገ መፈንቅለ መንግስት ሲሉ ጠርተዉታል፡፡

በሌላ መረጃ የፑቲንን የስልጣን ዘመን ማራዘም በመቃወም እንዲሁም በጸረ ሙስና ትግሉ የሚታወቀዉ አሌክሲ ናቫሊን በኮሮና ቫይረስ ተጥቅቶ ከማረሚያ ቤት ወደ ህክምና ስፍራ ማምራቱ ተሰምቷል፡፡አሌክሲ ናቫሊን ነርቭን በሚመርዝ ንጥረ ነገር ባለፈዉ ዓመት መመረዙ ይታወሳል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *