መደበኛ ያልሆነ

ዛሬ መጋቢት 28፤2013-የሰብአዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በሶማሊ ክልል የሚገኙ ፖሊስ ጣቢያዎች እና ማረሚያ ቤቶች ማሻሻያዎች ያስፈልጓቸዋል አለ፡፡

ኮሚሽኑ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ በጅግጅጋ ከተማ ካውንስል ፖሊስ መምሪያ በተለምዶ ሃቫና ተብሎ በሚታወቀው የተጠርጣሪዎች ማቆያ እና ቀበሌ 04 አቅራቢያ የሚገኘው የካውንስሉ ማቆያ የተጠርጣሪዎች አያያዝ እጅግ አሳሳቢ ነው ብሏል፡፡

ኮሚሽኑ መግለጫውን ለማውጣት መጋቢት 13 ቀን 2013 ዓ.ም. በጅግጅጋ ከተማ ፖሊስ ጣቢያዎች ያደረገውን ፈጣን ክትትል፤ ከእስረኞች፣ ከፖሊስ መምሪያዎች፣ ከማረሚያ ቤት ኃላፊዎች፣ እነዲሁም ከሌሎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመወያየት ያገኛቸውን መረጃዎች በግብአትነት ተጠቅሟል፡፡

በእስርቤቶቹ ተጠርጣሪዎች ንጽህናቸው ባልተጠበቀና በተጨናነቁ ክፍሎች ውስጥ ለጤና ጎጂ በሆነ አያያዝ ውስጥ እንደሚገኙ የኮሚሽኑ መግለጫ ያሳያል፡፡ ከ18 ዓመት በታች ያሉ ህጻናትን ጨምሮ በርካታ ተጠርጣረዎች በጊዜው ፍርድቤት አለመቅረባቸውን፣ ቤተሰብ እንዳይጎበኛቸው እንደተከለከሉ፣ ድብደባ እንደደረሰባቸው ከታሳሪዎች አሳማኝ ምስክርነት ተቀብሏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *