መደበኛ ያልሆነ

መጋቢት 29፤2013-በብራዚል ለመጀመሪያ ጊዜ ከ 4ሺህ በላይ ሰዎች በአንድ ቀን ውስጥ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው አለፈ

በትላንትናው እለት ብቻ በብራዚል የ 4,195 ሰዎች ህልፈት በቫይረሱ የተመዘገበ ሲሆን ፣ በመላው ሀገሪቱ የሟቾች ቁጥር ከ 337ሺ ተሻግሯል፡፡

በብራዚል የሚገኙ ሆስፒታሎች በታማሚዎች ብዛት የተጨናቀቁ ቢሆንም ፣ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ጄር ቦልሶናሮ አሁንም እንቅስቃሴን የሚከለክል ህግ እንዳይተገበር ከልክለዋል፡፡

የፅኑ ህሙማን መከታተያ ክፍሎች በመላው ሀገሪቱ ከ 90 በመቶ በላይ በታማሚዎች ተሞልቷል፡፡

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *