መደበኛ ያልሆነ

መጋቢት 29፤2013-አምነስቲ ኢንተርናሽናል ሩሲያ ቀስ በቀስ ናቫልኒን እየገደለች ነው ሲል አስታወቀ

የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቫላድሚር ፑቲኒን በመተቸትና በፀረ ሙስና አንቂነቱ የሚታወቀው አሌክሲ ናቫልኒ ላይ ጥቃት ከማድረስ ባለፈ በጊዜ ሂደት ህይወቱ እንዲያልፍ የማድረግ ስራን የሞስኮ መንግስት እየሰራ ነው ሲል ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታውቋል፡፡

የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ዋና ፀሃፊ የሆነችው ኮልአማርድ ቀስ በቀስ የሩሲያ መንግስት አሌክሲ ናቫሊንን የማስወገድ ስራ እየሰራ ነው ብላለች፡፡ ይህ ደግሞ የግለሰቡን የመኖር መብት የሚጋፋ ብለውታል፡፡

አሌክሲ ናቫሊን በኮሮና ቫይረስ ተጠቅቶ ከማረሚያ ቤት ወደ ህክምና ስፍራ እንዲያመራ ተደርጓል፡፡ ነርቭን በሚጎዳ ንጥረ ነገር ባለፈው ዓመት መመረዙም አይዘነጋም፡፡

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *