መደበኛ ያልሆነ

መጋቢት 29፤2013-ዋይት ሃውስ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ፓስፖርት ውድቅ አደረገ

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መዛመትን ለመከላከል የኮሮና ቫይረስ ፓስፖርትን ለእንቅስቃሴ መያዝ እንደ አስገዳጅ ህግ ለማውጣት እየተንቀሳቀሱ ቢሆንም የግለሰቦች ነፃነት የሚጋሩና አግላይ ነው በሚል እየተተቸ ይገኛል፡፡

አሜሪካ የኮሮና ቫይረስ ፓስፖርት ዜጎች ለመንቀሳቀስ የግድ ያስፈልጋቸዋል የሚለውን እንደማትደግፍና የዜጎችን መብት የሚጋሩ መሆኑን አሣውቃለች፡፡

አሜሪካ ከ 550ሺ በላይ ዜጎቿን በቫይረሱ ተነጥቃለች፡፡ የዋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ጆን ሳኪ ዜጎች መከተባቸውን የሚያሳይ መረጃ ይዘው መጓዝ እንዳለባቸው የሚያስገድደውን ህግ መንግስት አይደግፍም ብላለች፡፡

እንግሊዝና የአውሮፓ ህብረት የኮሮና ፓስፖርትን ተግባራዊ ለማድረግ እየሰሩ ሲሆን እስራኤል ‹‹አረንጓዴ ማለፊያ›› በማለት ለተከተቡ ዜጎቿ እየሰጠች ነው፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *