መደበኛ ያልሆነ

መጋቢት 30፤2013-በደቡብ ኮርያ ገዢው ፓርቲ በሁለት ወሳኝ ከተሞች ምርጫ ተሸነፈ

የደቡብ ኮርያ ገዢው ዲሞክራቲክ ፓርቲ ቁልፍ በሚባሉት ሴኦል እና ቡሳን ከተሞች ምርጫ ተሸንፏል።የተቃዋሚው የፒፕልስ ፖወር ፓርቲ እጬዎች በሰፊ ልዩነት አሸንፈዋል።

የገዢው ፓርቲ የሴኦል እና ቡሳን ከተሞች ከንቲባዎች በወሲባዊ ጥቃት ሙከራ ክስ ቀርቦባቸው የነበረ ሲሆን ለሽንፈቱ እንደ ምክንያት ተወስዷል።

የገዢው ዲሞክራቲክ ፓርቲ እና የፕሬዝዳንት ሙን ጃ ኢን ተቀባይነት በባለስልጣናት የወሲብ ቅሌቶች ክስ፣በቤት ዋጋ መጨመር እና የገቢ ልዩነት አለመመጣጠን ወርዷል።

በቀጣይ ለሚደረገው ኘሬዝዳንታዊ ምርጫ የገዢው ዲሞክራቲክ ፓርቲ ሊፈተን እንደሚችል ይህ የከተማ ምርጫ ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *