መደበኛ ያልሆነ

መጋቢት 30፤2013-የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካህን ወሲባዊ ጥቃት የጨመረው ሴቶች በሚለብሱት ልብስ የተነሳ ነው በማለታቸው ከፍተኛ ትችት ተሰነዘረባቸው

የተገላለጠ አልባሳትን የሚለብሱ ሴቶች ቁጥር መበራከት ለወሲባዊ ጥቃት መጨመር ምክንያት ሆኗል ሲሉ የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካህን ተናግረዋ።ይህንን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግር የሰሙ የመብት ተሟጋቾች ካህን ለንግግራቸው ይቅርታ ይጠይቁ ብለዋል።

በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ካህን ይቅርታ እንዲጠይቁ የፊርማ ዘመቻ ጀምረዋል።

በፓኪስታን ወሲባዊ ጥቃት ለምን ጨመረ በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ በህንድ ቦሊውድና በአሜሪካ ሆሊውድ ተፅዕኖ የፓኪስታን ሴቶች ወድቀዋል፤የተገላለጠ ልብስን ማዝወተር ምክንያቱ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

በፓኪስታን በየእለቱ ቢያንስ 11 ሴቶች የአስገድዶ መደፈር ጥቃት እንደሚደርስባቸው ሪፖርት ይደረጋል።

ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያና በእስራኤል በተካሄደ ኤግዚብሽን ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች በእለቱ የለበሱት ልብስ ያልተገላለጠ አልባሳት ነበር።ይህን የተገላለጠ አልባሳት ለፆታዊ ጥቃት መጨመር እንደ ሰበብ ማቅረብ ተቀባይነት የሌለው ነዉ ሲሉ የመብት ተሟጋቾች ይተቻሉ።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *