መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 20፣2013-በህንድ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ 200ሺህ በላይ ሆነ

በትላንትናው እለት ብቻ በህንድ በቫይረሱ የ3,286 ሰዎች ህልፈት መመዝገቡን ተከትሎ በአጠቃላይ የሟቾቹ ቁጥር ከ 200ሺህ ተሻግሯል።

በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ በሀገሪቱ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ከ 2ሚሊዮን በላይ ሁኖ ተመዝግቧል።

በህንድ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ200 ሺህ በላይ ሁኖ በመብለጡ በአለማችን በኮሮና ቫይረስ ከፍተኛ ሞት ከተመዘገበባቸው ሀገራት አሜሪካ ፣ ብራዚል እና ሜክሲኮ በመቀጠል በአራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

በኒውደልሂ ከተማ ቀን እና ማታ አስከሬን የማቃጠል ስነስርዓት ያለ ፋታ እየተሰራ ይገኛል።

በህንድ መዲና ኒውደልሂ ብቻ 381 ሰዎች በ 24ሰዓት ውስጥ ህይወታቸውን አጥተዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *