መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 20፣2013-በአዊ በሁለት ሰዎች ላይ ጉዳት ያደረሰው ነብር ተገድሏል!

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር አየሁ ጓጉሳ ወረዳ በትላንትነው እለት ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ገደማ መነሻው ከየት እንደሆነ ያልታወቀ ነብር በሁለት ሰዎች ጉዳት አደረሰ።

ከጉዳት ሰለባዎቹ መካከል አንዱ ነዋሪነቱ አዘና ጉሲ የሆነ ግለሰብ ቀላል ገዳት የደረሰበት ሲሆን ሌላኛዋ ደግሞ ነዋሪነቷ አዘና 3ቱ ሰኞ ቀበሌ የሆነች ሴት ከባድ ጉዳት ደርሶባት በህክምና እየተረዳች ትገኛለች።

በተጨማሪም ነብሩ ወደ ገብያ በመውጣት ሌሎች ግለሰቦች ላይ ጉዳት ሊያደርስ ሲል በህብረተሰቡ ትብብር በተተኮሰው ጥይት ህይወቱ በማለፍ የሰው ህይወት ሊተርፍ መቻሉን ከአየሁ ጓጉሳ ወረዳ ኮሚኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያሳያል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *