መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 20፣2013-እኛ ከለቀቅን ማን ሊመራ ይችላል ሲሉ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ፈርማጆ ተናገሩ፤ የፕሬዝዳንቱ ስልጣን አይራዘምም!

የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ፈርማጆ The Buffalo ለተባለ ጋዜጣ በሰጡት ማብራሪያ ስልጣን እኛ ከለቀቅን ማን ሊመራ ይችላል ሲሉ ተናግረዋል።ሆኖም በሰላማዊ ምርጫ አሸናፊ አካል ካልተለየ ስልጣን ለማስረከብ ፍቃደኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ፕሬዝዳንት ፋርማጆ የስልጣን ዘመናቸው በወርሃ የካቲት ቢጠናቀቅም በሞቃዲሾ ቤተ መንግስት ለሁለት ዓመታት ስልጣናቸውን እንዲራዘም የታችኛው ምክር ቤት መወሰኑ ይታወሳል።ይህው ውሳኔ በፑንት ላንድና ጁባ ላንድ አስተዳደር ጨምሮ በሴኔቱ ውድቅ መደረጉ አይዘናጋን።

ይህንኑ ተከትሎ በሞቃዲሾ ከተማ ከባድ ውጥረትና በፕሬዝዳንቱ ታማኝ ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎቻቸው ዘንድ ግጭት ተቀስቅሷል።

ግጭቱ ያመጣውን ውጥረት ተከትሎ ፕሬዝዳንቱ በታችኛው ምክር ቤት ስልጣናቸውን እንዲያራዝሙ የተሰጠውን ድጋፍ ውድቅ ማድረጋቸውን በዛሬው እለት በሶማሊያ ብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው ተናግረዋል።

አዲስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንዲደረግ ጥሪ ማቅረባቸውን ተቃዋሚዎቻቸው ደግፈውታል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *