መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 25፤2013-አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ‘የምስራቅ አፍሪካ ምርጡ ዩኒቨርሲቲ’ ተባለ❗️

‘US News Global’ የተሰኘ ዓለም-አቀፍ ተቋም ባወጣዉ የ 2021 የዓለም ዩኒቨርሲቲዎች የደረጃ ሰንጠረዥ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን የምስራቅ አፍሪካ ‘ምርጡ ዩኒቨርሲቲ አንተ ነህ’ ብሎታል::

በዚሁ ተቋም ከምስራቅ አፍሪካ የቀዳሚነትን ክብር ያገኘዉ አዲስ አበባ ዪኒቨርሲቲ ከድፍን አፍሪካ 10ኛዉ ከመላዉ ዓለም ደግም 553ኛዉ ምርጥ ዩኒቨርሲቲ ተብሏል::

ዩኒቨርሲቲዉ ባለፈዉ ዓመት በዚሁ ተመሳሳይ ተቋም በተሰጠዉ ደረጃ ከምስራቅ አፍሪካ የሁለተኝ-ነትን ከዓለም ደግሞ የ 616-ኝነትን ስፍራ ነበር ያገኘዉ::

በ ‘US News Global’ ደረጃ ሰንጠረዥ ኬፕ-ታዉን ዩኒቨርሲቲ ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆኗል::

በአንፃሩ ብስራት ሬዲዮ እንደተረዳዉ በሪፖርቱ ተካተዉ ደረጃ ከወጣላቸዉ 1 ሺህ 500 የዓለም ምርጥ ዩኒቨርሲቲዎች ዉስጥ የአሜሪካዉ ሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የሁሉም አዉራ ተብሏል::

ሄኖክ አለማየሁ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *