መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 3፤2013-ሞያሌን የአፍሪካ ቀንድ ዱባይ ለማድረግ እየተሠራ ነው ተባለ!

በዛሬው እለት የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ከጋዜጠኞች ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል።በተያዘው ሳምንት ለአንድ ቀን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ የኢትዮጵያ የመጡት የኬንያው ፕሬዝዳንት ኧሁሩ ኬንያታ በተመለከት ከጋዜጠኞች ለተነሳው ጥያቄ አምባሳደሩ ምላሽ ሰጥተዋል።

ኢትዮጲያ ከኬንያ ጋር ያላትን የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ግንኙነት ከማጠናከር ባለፈ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ሰፊ ውይይት የተደረገበት መሆኑን አምባሳደር ዲና ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ እና ኬንያ ግንኙነት ከዚህም በላይ ነው ሞያሌን የአፍሪካ ቀንድ ዱባይ ለማድረግ እየተሰራ ስለመሆኑ አምባሳደር ዲና መናገራቸውን ብስራት ሬድዮ ሰምቷል።

ፕሬዝዳንቱ በቆይታቸው ከኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር በሁለትዮሽና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ምክክር አድርገዋል። የሀገራቱ ግንኙነት ጠንከር ያለ ስለመሆኑ በመግለጫው ተነስቷል።

በቤቴልሄም እሸቱ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *