መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 3፤2013-በህንድ በ24 ሰዓት ውስጥ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሣ የ6,148 ሰዎች ህይወት አለፈ!

በህንድ በ24 ሰዓት ውስጥ የተመዘገበው የሞት መጠን ከዚህ ቀደም በዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ከተባለው የሞት መጠን በእጅጉ የላቀ ሆኗል።ከዚህ ቀደም በዩናይትድ ስቴትስ የተያዘው የ24 ሰዓት ከፍተኛው የሞት መጠን 5,444 ነበር።

በ24 ሰዓት ውስጥ 6,148 ሰዎች በቫይርሱ ህይወታቸውን ማጣታቸውን የህንድ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።በመላው ህንድ በቫይረሱ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ353ሺ በላይ ሆኗል።

የህንድ መንግስት እስከ ቀጣዩ ዓመት ታህሳስ ወር ድረስ ከ2 ቢሊዮን በላይ ዶዝ ክትባቶች ሊያገኝ እንደሚችል አስታውቋል።የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በተያዘው ሳምንት እንዳስታወቁት ለሁሉም ህንዳዊያን አዋቂዎች ክትባቱን በነፃ ይቀርባል ብለዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *