መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 3፤2013-ባይደን ሩሲያ ከ ‹አጓጉል ድርጊቶች› እንድትታቀብ ሲሉ በመጀመሪያ ይፋዊ ጉዞ ጅማሯቸው አስጠንቅቀዋል!

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ለቡድን ሰባት የመሪዎች ጉባኤ ዩናይትድ ኪንግደም ይገኛሉ፡፡

ፕሬዝዳንቱ የመጀመሪያ ይፋዊ ጉዟቸውን ተከትሎ በመግለጫቸው ሩሲያ ሌሎችን በሚጎዳ ተግባር ላይ የምትሰማራ ከሆነ “ጠንካራ እና ትርጉም ያለው” መዘዞች ትጋፈጣለች ብለዋል፡፡

ባይደን በትራምፕ አስተዳደር የተበላሹ የሚሉትንና ከአሜሪካ አጋሮች ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር ያላቸውን ፍላጎት በግልፅ አሳይተዋል፡፡

በአዲሱ “አትላንቲክ ቻርተር” ዙሪያ ለመስማማት ከጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ጋርም ይገናኛል፡፡ ስምምነቱ እ.ኤ.አ.በ 1941 በዊንስተን ቸርችል እና ፍራንክሊን ሩዝቬልት መካከል ስምምነት የተደረገበት የአየር ንብረት ለውጥን እና ደህንነትን ጨምሮ ተግዳሮቶች ላይ ያተኮረ ዘመናዊ ስሪት ይሆናል

በስምንት ቀናቱ የአውሮፓ ጉብኝት ባይደን ከንግስቲቷ ጋር በዊንድሶር ካስትል ፣ በቡድን ሰባቱ ሀገራት ስብሰባ ላይ ይታደማሉ እንዲሁም በፕሬዝዳንትነት ለመጀመሪያ ጊዜ በኔቶ ጉባኤው ላይ የሚሳተፍ ይሆናል፡፡

በጉብኝቱ መባቻ ባይደን ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በጄኔቫ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *