መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 3፤2013-ኔቶ ወደ ኢትዮጲያ ሊዘምት ነው በሚል የሚሰራጨው መረጃ የሀሰት ነው ተባለ

በዛሬው እለት የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ከጋዜጠኞች ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል።የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን/ኔቶ/ ወደ ኢትዮጲያ ሊዘምት ነው ስለሚባለው መረጃ ከጋዜጠኞች ለተነሳው ጥያቄ አምባሳደሩ ምላሽ ሰጥተዋል።

የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን ኔቶ ወደ ኢትዮጲያ ሊዘምት ነው የሚባለው ነገር የተሳሳተ መረጃ ነው ፤ኢትዮጵያ ነጻነት ያላት ሉዐላዊ ሃገር ናት በዚህ ጉዳይ አትደራደርም ሲሉ አምባሳደር ዲና መናገራቸውን ብስራት ሬድዮ ሰምቷል።

በሌላ በኩል የሱዳን ጉዳይን በተመለከተ እኛ ለሱዳን ህዝብ ጥሩ ነን ክፉ ለገር አንመኝም በድንበሩ ጉዳይ ላይ ግን ምንም አዲስ ነገር የለም የእኛ አቋም እንደ በፊቱ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በፌደራል መንግስትና በህወሓት ኃይሎች መካከል ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎ የሱዳን ጦር የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ በመግባት መሬት መያዙን ኢትዮጲያና ሱዳን ከዚህ ቀደም የነበረውን መልካም ግንኙነት እንዲሻክር ያደረገ መሆኑ አይዘናጋም።

የኢትዮጵያ መንግስት የድንበር አለመግባባት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ያለውን ፍላጎት ማሳወቁም ይታወሳል።

በቤቴልሄም እሸቱ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *