መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 3፤2013-የሞስኮ ፍርድ ቤት ከተቃዋሚው አሌክሲ ናቫልኒ ጋር ትስስር አላቸው ያላቸውን ተቋማት አገደ

በእስር ላይ የሚገኘው የክሪምሊ አቀንቃኝ አሌክሲ ናቫሊ ጋር ግንኙነት አላቸው ያላቸውን ተቋማት የሞስኮ ፍርድ ቤት እንዲዘጉ ያለው ፣ እነሱን እንደ “አክራሪ” ፈርጆ ነው፡፡

እነዚህ ድርጅቶች በመንግስት ባለስልጣናት ላይ ጥላቻ እና ጠላትነት እንዲነሳሳ የሚያደርጉ መረጃዎችን ከማሰራጨት ባለፈ ፅንፈኛ እርምጃዎችን ሲወስዱ እንደነበር የዓቃቤ ሕግ ቃል አቀባይ አሌክሲ ዣፍያሮቭ ከፍርድ ቤቱ ውጭ ተናግረዋል፡፡ የሚስተር ናቫልኒ ጠበቆች በበኩላቸው ውሳኔውን ይግባኝ እንደሚሉ ተናግረዋል ፡፡

መንግስትን የሚቃወመው ናቫልኒ ነርቭን በሚጎዳ ኬሚካል ከደረሰበት ጥቃት ከጀርመን ህክምናውን ጨርሶ ሀገሩ እንደተመለሰ በሩሲያ መንግስት ለእስር መዳረጉ ይታወሳል፡፡

ናቫልኒ በእስር ላይ ሁኖም ወደኋላ እንደማያፈገፍግ ሲገልፅ ቆይቷል፡፡ ደጋፊዎቹም ተቃውሟቸውን እንዲገፉበት መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

በናቫሊ ኢንስታግራም ገፅ በተላለፈው መልዕክትም የትም አንሄድም ሲሉ ተቃውሟቸውን ገልፀዋል፡፡ “ይህንን ፈጭተን ፣ ነገሮችን በመለየት ፣ በመለወጥ እና በዝግመተ ለውጥ እንሰራለን ፣ እኛ እንጣጣማለን፣ ከአላማችን እና ከሃሳባችን ወደ ኋላ አንመለስም ፡፡ ይህች ሀገራችን ናት ሌላ የለንም” ብለዋል፡፡

የሩሲያ የፓርላመንት ምርጫ በወርሃ መስከረም የሚከናወን ሲሆን ገዢው ፓርቲ ድምፅ ሊያጣ እንደሚችል እየተነገረ ይገኛል፡፡ የናቫልኒ ደጋፊዎች ምርጫው ላይ ለመሳተፍ ማቀዳቸውም ተነግሯል፡፡

ሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *