መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 4፤2013-አንዲት ጣሊያናዊት ሴት ከ10 ወራት በኋላ ከሰመመን(ኮማ)ነቃች

የ37 ዓመቷ ክሪስቲና ሮሲ ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር ውስጥ በልብ ህመም ስትሰቃይ የሰባት ወር ነፍሰ ጡር ነበረች ፡፡ሴት ልጇን ካትሪና በአስቸኳይ ክፍል ብትገላገልም በአንጎል ጉዳት ሳይሆን አልቀረም በተባለ የጤና እክል ግን ለ10 ወራት በሰመመን ለማሳለፍ ተገዳለች፡፡

አሁን ከሰመመን የነቃች ሲሆን የመጀመሪያ ቃሏ “ማማ”(እማ) ስትል መናገሯን ባለቤቷ አስታዉቋል፡፡ባለቤቷ ጋብሪየል ሱቺ እኛ ይህንን አልጠበቅንም ነበር ከብዙ ስቃይ በኋላ እውነተኛ ደስታ ሆኗል ስሜቱን አጋርቷል፡፡

የመጀመሪያዋን ቃል ስትናገር ባለቤቷም ሆኑ ወላጅ እናቷ ከጎኗ ነበሩ ፡፡የጥንዶቹ ሴት ልጅ በወሊድ ወቅት ኦክስጅን እጥረት ስላጋጠማት በርካታ ወራትን በሆስፒታል ውስጥ ቆይታለች፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *