መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 8፤2013-በህንድ ለ11 ዓመታት ከቤተሰቦቿ ቤት የጠፋችው ሴት በጎረቤት ቤት ከነበረ ልጅ ጋር ተደብቃ ትኖር እንደነበር ተደረሰባት

እ.ኤ.አ በ2010 ሳጂታ ከቤተሰቦቿ መኖሪያ ቤት በድንገት ትጠፋለች።ሁኔው በጊዜው አስደንጋጭ የሆነባቸው ቤተሰቦቿ ልጃቸውን ለማግኘት ብዙ አፈላልገው አልተሳካላቸውም።

ወይ ሞታለች አልያም ርቃ ተጉዛለች የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል።ሆኖም ሳጂታ ግን ከቤተሰቦቿ መኖሪያ ቤት በ500 ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ራማን ከተባለ ግለሰብ ጋር በፍቅር ወድቃ ለ11 ዓመታት ተሸሽጋ ኖራለች።

ሁለቱ ጥንዶች ለ11 ዓመታት በፍቅት ሲኖሩ የሁለቱም ቤተሰቦች የሚያውቁት መረጃ አልነበራቸውም።ራማን ይኖርበት ወደነበረው ክፍል ቤተሰቦቹ እንኳን ለመግባት ሲሞክሩ በድንገት እንደ አእምሮ ህመምተኛ ቁጡና አስቸጋሪ ባህሪን ያሳይ ነበር።

ራማን በሙያው ቀለም ቀቢ ሲሆን ወደ ስራ ሲያመራ ሳጂታን ላይ በር ቆልፎ ነበር።በዚህች አንድ ክፍል ውስጥ ከእርሱም ቤተሰቦች የተደበቀችው ሳጂታ በባሏ ድጋፍ ሁሉም ነገሯ በዚህ ክፍል ውስጥ የተገደበ ነበር።

ራማን ለ11 ዓመታት ሳጂታን በቤተሰቡ ቤት እነርሱም ሳያውቁ ሸሽጎ ቢያቆያትም ከ3ወር በፊት ግን ጥንዶቹ ቤት ይከራያሉ።ራማን በድንገት ከቤቱ በመጥፋቱ ቤተሰቦቹ ለፖሊስ ያሳውቃሉ።

ፖሊስ ባደረገው ክትትል ራማ በተከራየው ቤት ከ11 ዓመታት በፊት ጠፍታለች ከተባለችው ሳጂታ ጋር እንደሚኖሩ ደርሶባቸዋል።እምነታችን የተለያየ ደግሞም በሁለታችንም ቤተሰቦች ጋብቻችን ሊፈቀድ የማይችል በመሆኑ ይህንን መንገድ መረጥን ሲሉ ለፖሊስ ቃላቸውን ሰጥተዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *