መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 13፣2013-ስለ ድምፅ መስጫ ቀን በጥቂቱ

በድምጽ መስጫ ቀን የተከለከሉ ተግባራት ምን ምን ናቸው?

• ማንኛውም ሰው ከምርጫ ጣቢያው 200 ሜትር ዙሪያ መለስ ርቀት ውስጥ በስካር መንፈስ ውስጥ ሆኖ፣ የጦር መሣሪያ ይዞ ወይም በሌላ በማናቸውም ፀጥታን በሚያደፈርስ ሁኔታ ውስጥ መገኘት የለበትም
• መራጭ ያልሆኑና ድምፅ የሰጡ ሰዎች በምርጫ ጣቢያው ውስጥ መገኘት የለባቸውም
• ማንኛውም ሰው ያለፈቃድ ወደምርጫ ጣቢያው በመግባት ወይም በምርጫ ጣቢያው ግቢ ውስጥም ሆነ ውጭ የምርጫውን እንቅስቃሴ ማወክ ወይም ማደናቀፍ ወይም ምንም አይነት የምርጫ ቅስቀሳ እንቅስቃሴ ማድረግ የለበትም

ወደ ምርጫ ጣቢያ የማይገቡ ነገሮች ምንድናቸው?

• ማንኛውም ሰው እንደ በራሪ ወረቀት፣ ፖስተር እና በሌሎች አጭር ጽሁፍ መልክ የተዘጋጁ የምርጫ ቅስቀሳ ሰነዶችን ይዞ ወደ ምርጫ ጣቢያው መግባት አይችልም፡፡

• ማንኛውም ሰው የጦር መሳሪያ ወይም እንደጩቤና ሴንጢ የመሳሰሉ ስለትነት ያላቸውን ወይም እንደየአካባቢው ሁኔታ ለሀይል መጠቀሚያነት የሚውሉ እንደዱላ፣ አለንጋ ፣ ቁራጭ እንጨት ወይም ብረት ወይም ሌላ ማንኛውንም ተቀጣጣይ ወይም የሚፈነዳ ጠጣር ወይም ፈሳሽ ነገር ይዞ ወደ ምርጫ ጣቢያ መግባት የለበትም።

• ከላይ የተዘረዘሩትን የተከለከሉ ነገሮች ወደምርጫ ጣቢያ ይዞ የመጣ መራጭ የምርጫ ጣቢያው የሰልፍ አስከባሪ በሚሰጠው መመሪያ መሰረት በአደራ አስቀምጦ መግባት አለበት።

ምንጭ፦የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *