መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 15፤2013-የጋዳፊ የአውሮፕላን ቤተመንግስት ይባል የነበረው አውሮፕላን ወደ ሊቢያ ተመለሰ

የቀድሞ የሊቢያ መሪ ሙሃመር ጋዳፊ የግል አውሮፕላን ለጥገና እና ለደህንነት በሚል በፈረንሳይ ለዓመታት የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ትሪፖሊ እንደሚገኝ ተሰምቷል።ይህው ግዙፍ አውሮፕላን ኤር ባስ ኤ340 የሚሰኝ ሲሆን ትሪፖሊ ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው ሚቲጋ ኤርፖርት አርፏል።

የሊቢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዲቤይህ ኤርፖርት በመገኘት አውሮፕላኑን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። አስፈላጊውን የጥገናና ሌሎች የአውሮፕላን ወጪ የሊቢያ ጊዚያዊ መንግስት የሸፈነ ሲሆን ለሀገሪቱ ጥቅም እንደሚውል ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

የሊቢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዲቤይህ እንደተናገሩት የጋዳፊ ንብረት የነበሩ 14ጄቶች ወደ ሀገር ውስጥ እንዲመለሱ መንግስታቸው እየሰራ ሲሆን 12ቱን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ቀነ ቀጠሮ ተይዞላቸዋል።

የጋዳፊ ጄቶች በትሪፖሊ ሰማይ ላይ ሲበሩ ዝቅ ብለው ሲሆን ከማረፋቸው በፊት አየር ላይ ክብ ይሰሩ ነበር።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *