መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 12፤2013-የነዳጅ አምራች ሀገራት ዋጋውን ለመቆጣጠር ስምምነት ላይ ደረሱ

ነዳጅ አምራች ሀገራት ዋጋ ለመቀነስ እና በዓለም ኢኮኖሚ ላይ የሚደርሰውን ጫና ለማቃለል በማሰብ ምርታቸውን ለማሳደግ ተስማምተዋል።የኦፔክ አባላት እና እንደ ሩሲያ ያሉ አጋር ሀገራት ከነሀሴ ወር ጀምሮ የምርቱን አቅርቦት በማሳደግ ዋጋው እንዲቀንስ ያደርጋሉ።

ያልተጣራው ድፍድፍ ነዳጅ በበርሜል በተያዘው ዓመት 43በመቶ ከፍ ያለ ሲሆን በ74 የአሜሪካ ዶላር እየቀረበ ይገኛል።ባለፈው አመት በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ የነዳጅ ፍላጎትና ዋጋ በመቀነሱ በየቀኑ 10 ሚሊዮን በርሜል ምርት በየቀኑ ለመቀነስ የኦፔክ አባላት ስምምነት ላይ ደርሰው እንደነበር ይታወሳል።

ሆኖም በተያዘው ዓመት እንቅስቃሴ ሲጀመር ዋጋው መጨመሩ እና በአንዳንድ ሀገራት ግሽበት እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል።የነዳጅ አምራች ሀገራት የምርት ቅነሳውን ለማድረግ ሲያቅዱ ቆይተዋል፤ሆኖም ግን በሳዑዲ እና በኢምሬትስ መካከል የተፈጠረው ውዝግብ እቅዱ እንዲዛባ ምክንያት ሆኖ ቆይቷል።

ያልተለመደው የሁለቱ አጋር ሀገራት ውዝግብ በኦፔክ ውስጥ አለመረጋጋት ሊያስከትል እንደሚችል ተሰግቷል።ሁለቱ ሀገራት 50 በመቶ የአለም ነዳጅ አቅራቢ ናቸው።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *