መደበኛ ያልሆነ

ጷግሜን 2፤2013-በአዳማ ከተማ በ2013 ዓመት ሶስት ሰዎች በጅብ ተበልተው ህይወታቸው እንዳለፈ ተነገረ

በአዳማ ከተማ መስተዳድር በመገባደድ ላይ በሚገኘው የ2013 ዓመት ሶስት ሰዎች በጅብ በመበላታቸው ህይወታቸውን አጥተዋል።የሶስቱ ሰዎች ህይወት ያለፈው በከተማዋ በሚገኙት ቦኩ ክፍለ ከተማ ቦኩ ሸነን ቀበሌ፣ በቦሌ ክፍለ ከተማ እና ዳቤ ክፍለ ከተማ ዳቤ ሹሉቄ ቀበሌ ውስጥ በደረሰባቸው የጅብ ጥቃት ነው፡፡

የጅብ ጥቃቱን ተከትሎ የአንድ ሴት እና ሁለት ወንዶች ህይወት አልፏል።ከነዚህ መካከል ለእንግድነት ከወላጅ እናቱ ጋር የሄደ የ 18ወር ህፃን በጅብ ተበልቷል።

በአዳማ ከተማ መስተዳድር ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ረዳት ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት ሶስቱም ነዋሪዎች ጥቃቱ የተፈፀመባቸው በምሽት ነው፡፡

ሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *