
በሰሜን ምስራቃዊ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ግዛቶች የማጅራት ገትር በሽታ መቀስቀሱ በይፋ የታወጀ ሲሆን እስካሁን 120 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል። በሀገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የማጅራት ገትር በሽታ መከሰቱ የታወቀው በሀምሌ ወር ነበር።
የበሽታው መቀስቀስን ፈታኝ ያደረገው የአካባቢው ማህበረሰብ በሽታውን ከጥንቆላ ጋር በማያያዙ እንደሆነ የአለም የጤና ድርጅት አስታውቋል።ከህክምና ይልቅ አንዳንድ ህሙማን ከቦታ ቦታ በመቀየር በሽታውን ለመሸሽ መሞከራቸው ችግሩን አባብሶታል።
በአፍሪካ ከኢትዮጵያ እስከ ሴኔጋል ያሉ ሀገራት የማጅራት ገትር የሳህል መቀነት በመባል ይታወቃሉ።26 የአፍሪካ ሀገራትን የሚያካትት ሲሆን በሽታው ከወርሃ ጥር እስከ ሀምሌ ባለው ጊዜ እነዚህን ሀገራት ተጋላጭ ያደርጋል።
በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተከሰተው የማጅራት ገትር በሽታ ላይ የተወሰደው ናሙና በፈረንሳይ ላብራቶሪ መመርመር የተቻለ ሲሆን ለበሽታው መነሻ ምክንያት የሆነው ቫይረስ ወረርሽኝ ሊያስከትል እንደሚችል ተጠቁሟል።
በስምኦን ደረጄ