መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 3፤2014-በኢትዮጵያ በአንድ ሳምንት ውስጥ 166 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው አጥተዋል

የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገዉ መረጃ መሰረት በአንድ ሳምንት ውስጥ 166 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ወረርሽ የተነሳ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡በአጠቃላይ በሳምንት ውስጥ በቫይረሱ የተያዙ 8120 ሺህ በኢትዮጲያ ስለመጠቃታቸው ሪፖርት ተደርጓል፡፡በአሁኑ ሰአት በኢትዮጵያ ከ2.7 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ኮሮና ቫይረስ ክትባት መከተባቸውን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በእለታዊ መረጃዉ አስታዉቋል፡፡

ከቀናት በፊት በኢትዮጵያ ዴልታ የተሰኘው የኮሮና ቫይረስ ዝርያ መኖሩ ይፋ መደረጉ ይታወሳል፡፡ዴልታ የተሰኘው ዝርያ በስርጭት ፍጥነት ቀደም ብሎ ከነበረው አልፋ ከተሰኘው ዝርያ በ2 እጥፍ እንደሚበልጥ የጠቆሙት ዶ/ር ሊያ ታደሰ በቫይረሱ የመያዝ ምጣኔ 20 በመቶ መድረሱን አማካይ የሞት ምጣኔም በቀን 16 ሰዎች መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በኢዮጲያ ውስጥ የኮሮና ቫይረስ በሽታ በከፍተኛ ሁኔታ መስፋፋት በመቀጠሉ የጤና ሚኒስቴር ከጥቂት ሳምንት በፊት በሽታውን ለመከላከል መወስድ ስላለባቸው የጥንቃቄ እርምጃዎች ያወጣውን መመሪያ በማሻሻል በጥብቅ ተግባራዊ እንዲሆን ማዘዙ ይታወሳል።

ቤተልሄም እሸቱ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *