መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 3፤2014-በኦሮሚያ ክልል በአንድ ሳምንት ውስጥ በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች የ30 ሰዎች ሕይወት አልፏል❗️

ከጳጉሜ 1 ቀን 2013 እስከ መስከረም 2 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ባጋጠሙ የትራፊክ አደጋዎች የ30 የሰዎች ህይወት ሲያልፍ ፤ በ15 ሠዎች ላይ ከባድ ፣ በ3 ሰዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት እንዲሁም 6 የንብረት ውድመት ደርሷል፡፡ ይህም በገንዘብ ሲተመን ሦስት ሚሊየን አራት መቶ ሺ ብር በላይ እንደሚገመት ተጠቁሟል፡፡

አደጋዎቹ በምስራቅ ሀረርጌ ሜታ ፣በሰሜን ሸዋ ወረጃርሶ ፣ ቦረና ዞን ቢቶ ፣በኦሮሚያ ልዩ ዞን ሱሉልታ እና ሰበታ ፣ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ወሊሶ ፣ምስራቅ ባሌ ቡርቃ ቡሉቃ ወረዳዎች ደርሰዋል::በተጨማሪም በአዳማ ፣ቢሾፍቱ ፣ ባቱ ከተማዎች አደጋዎቹ ደርሰዋል፡፡

አደጋዎቹ ከንጋቱ 3 ሠዓት እስከ ምሽቱ 11 ሰዓት የደረሱ ሲሆን አብዛኛዎቹ አደጋዎች በከባድ ተሽከርካሪ የተከሰቱ መሆናቸው ተገልፆል፡፡የአደጋዎቹ ሁኔታ ካለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር የጨመረ ሲሆን ፤ መንስኤዎቹም ከፍጥነት በላይ ማሽከርከር፣የጥንቃቄ ጉድለት እና ለእግረኛ ቀድሚያ አለመስጠት መሆኑን በኦሮሚያ ፖሊስ የትራፊክ ደህንነት እና ቁጥጥር ክፍል ባለሙያ ሳጅን የባሌወርቅ ደጀኔ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

ሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *