መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 3፤2014-የፓሪስ ከተማ ከንቲባ አኔ ሂዳልጎ ለፈረንሳይ ፕሬዝዳንታዊ እጩ ሆና ቀረበች

የፓሪስ ከተማ ከንቲባ የሆነችዉ አኔ ሂዳልጎ በተያዘዉ ዓመት በሚካሄደዉ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንደምትወዳደር አስታዉቃለች፡፡ ከስፔን የፍራንሲስኮ ፍራንኮን አምባገነንነት አስተዳዳር ከሸሹ የስፔን ስደተኞች የተወለደችዉ የ62 ዓመቷ የሶሻሊስት ፓርቲን ዕጩ እንደምታሸንፍ ሰፊ ግምት ከወዲሁ ተሰጥቷታል፡፡

ሆኖም ግን የፓሪስ የመጀመሪያዋ ሴት ከንቲባ የፈረንሣይ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ለመሆን በብሔራዊ ደረጃ ሰፊ ቅስቀሳ ማድረግ ይኖርባታል። በትላንትናዉ ዕለት አኔ ሂዳልጎ ለፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንደምትወዳደር ይፋ ካደረገች ከደቂቃዎች በኋላ ተቀናቃኟ የቀኝ ዘመሟ መሪ ማሪን ለፔን በደቡባዊ ፈረንሳይ የፍሬጁስ ከተማ ሦስተኛውን የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዘመቻ ጀምራለች፡፡

ኢማኑኤል ማክሮን በአየር ንብረት ዙርያ የገቡትን ቃል አለመጠበቃቸዉ እያስተቻቸዉ ሲሆን አኔ ሂዳልጎ ፈረንሳይን ወደ ዝቅተኛ የካርበን ልቀት ለማስገባት እንደምትሰራ ተናግራለች፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *