መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 4፤2014-በአንድ ወር ውስጥ ከ201 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ለታላቁ የኢትዮጲያ ህዳሴ ግድብ ተሰበሰበ

ከሃምሌ 1 ቀን 2013 እስከ ነሃሴ 1 ቀን 2013 ዓ.ም ከሀገር ውስጥ እና ከዉጪ ሀገር ቦንድ ሽያጭ እና ስጦታ ፣የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል የስጦታ አካውንት እና ከ8100 አጭር የሞባይል መልእክት በአጠቃላይ ከ201 ሚሊዮን ብር ገቢ መገኘቱን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ጽ/ቤት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ሃይሉ አብርሃም በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በነሃሴ ወር ደግሞ ከ96 ሚሊዮን ብር በላይከሀገር ውስጥ እና ከዲያስፖራ ማህበረሰብ እንዲሁም ከልዩ ልዩ ገቢዎች ገቢ መገኘቱ ተጠቁሟል፡፡

ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ቦንድ አስተዳደር ከፋይናንሻል ሪፖርት ምንጮች እና የህዳሴ ግድብ ቦንድ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የተገኙት መረጃዎች እንደሚያመላክቱት ግድቡ ከተጀመረ ጀምሮ በአጠቃላይ ከ 15ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን አቶ ሃይሉ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።

ቤተልሄም እሸቱ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *