መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 4፤2014-የባለስልጣኑን መስሪያ ቤት መታወቂያ በህገ ወጥ መልኩ አሰርተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 8 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የአዲስ አበባ ከተማ የምግብ፣ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን የአዲስ አመት መለወጫእና የመስቀል በዓል ቅድመ ዝግጅት በሚካሄድበት ወቅት ምግብን ከባእድ ነገር ጋር መቀላቀል፣የአገልግሎት ዘመን ያለፈባቸው መጠጦች አቅርቦት ፣የህገወጥ እርድ በስፋት እንደሚስተዋል አስታዉቋል፡፡

በመሆኑም ይህንን ተጠቅመው ህገ-ወጥ ተግባራት የሚበራከቱበት ወቅት በመሆኑ፤ የህዝብ ንቅናቄ በአስሩም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ 120 ወረዳዎች መከናወኑ ተገልፆል፡፡

በዚህ ንቁ ህዝባዊ ተሳትፎ ላይ 8 ግለሰቦች በልደታ በጉለሌና ኮልፌ ክ/ከተሞች የባለስልጣን መ/ቤቱ መታወቂያ አስመስለው በማሰራት ተቆጣጣሪ ነን በማለት ሲያጭበረብሩ በህብረተሰቡ ጥቆማ ተይዘው በህግ ሂደት ላይ እንደሚገኙ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለብስራት በላከዉ መግለጫ አስታዉቋል፡፡

እንዲሁም በስራ ላይ ባለመገኘትና የተሰጠውን ስራ በአግበቡ ባለመወጣት በልደታ 5 በቂርቆስ 2 በአዲስ ከተማ በማእክል ፤ በአቃቂ ቃሊቲ አንድ አንድ በድምሩ 10 ባለሙያዎች የጽሁፍ ማስጥንቀቂያ እርምጃ ተወስዶባቸዋል፡፡በተጨማሪም በአመቱ በባለስልጣኑ የስነ ምግባር ኮሚቴ 60 የስነ ምግባር ችግር አቤቱታን ውሳኔ ለመስጠት ታቅዶ 52ቱ ውሳኔ ያገኘ ሲሆን በአፈጻጸም 87 በመቶ ተከናዉኗል፡፡

ኤደን ሽመልስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *